ንግድ ባንክ ተከላካይ አስፈርሟል

በፕሪምየር ሊጉ ጠንካራ ጉዞን እያደረገ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ባደገበት ዓመት ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ሊጉን እየመራ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሁለተኛው ዙር ቀጣይ ጨዋታዎች ላይ አለብኝ ባለው ክፍት ቦታ በሁሉም የመከላከል ሚና ላይ የሚጫወተውን ተጫዋች ወደ ስብስቡ አካቷል።

ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች የመስመር እና የመሐል ተከላካይ ተመስገን ተስፋዬ ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ ቡራዩ ከተማ ፣ ወሎ ኮምቦልቻ ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፣ ሶዶ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን የተጫወተው ተከላካዩ ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ያለፉትን ስድስት ወራት አሳልፎ በስምምነት ከተለያየ በኋላ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና ኢትዮጵያ መድን ያሰለጠኑትን አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በይፋ ተቀላቅሏል።