ከፍተኛ ሊግ | ነገሌ አርሲ አራት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በከፍተኛ ሊጉ የምድብ ለ ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነው ነገሌ አርሲ ቡድኑን ለማጠናከር አራት ተጫዋቾችን አስፈርሟል።

በአሰልጣኝ በሽር አብደላ መሪነት በተከታታይ ዓመታት በከፍተኛ ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ እየሆነ የሚገኘው እና በዘንድሮው የከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ስር ተደልድሎ የመጀመሪያውን ዙር ከመሪው አርባምንጭ በመቀጠል በ28 ነጥቦች ዙሩን የቋጨው ነገሌ አርሲ በሁለተኛው ዙር ተጠናክሮ ለመቅረብ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን በሁለተኛው የዝውውር መስኮት ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

ከሀዋሳ ወጣት ቡድን እስከ ዋናው ድረስ ግልጋሎት በመስጠት በኋላ ከጉዳት መልስ በወራቤ እና ቡታጅራ ያሳለፈው አጥቂው ገብረመስቀል ዱባለ ፣ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ከተገኘ በኋላ በጅማ አባጅፋር ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና ወራቤ የተጫወተው የመስመር አጥቂው ምስጋናው መላኩ ወደ ቀድሞው ክለቡ የተመለሰበት ዝውውር ሲያጠናቅቅ ፣ በአጥቂ ቦታ ላይ በሾኔ ከተማ ፣ ደቡብ ፓሊስ ፣ ሺንሺቾ እና ጋሞ ጨንቻ ቆይታ የነበረው ምንስተኖት ታምሬ እንዲሁም በመቐለ 70 እንደርታ ፣ ቂርቆስ እና ደብረብርሃን በተከላካይ አማካይ ቦታ ላይ በመጫወት የሚታወቀው ፍፁም ተስፋማርያም ቡድኑን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራሚ ተጫዋቾች ሆነዋል።