ሀምበሪቾዎች የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀዋል

ሁለት አማካዮች ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚመልሳቸው ዝውውር አገባደዋል።

በአዲሱ አሰልጣኛቸው ተመስገን ዳና እየተመሩ የለቀቁባቸው ተጫዋች ለመተካት በእንቅስቃሴ ላይ የቆዩት ሀምበሪቾዎች የሁለት ተጫዋቾች ዝውውር አጠናቀዋል።

ቡድኑን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው እና ካለፈው የውድድር ዓመት ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን ሲጫወት የቆየው አማካዩ በኃይሉ ተሻገር ነው ፤ ከዚህ ቀደም በኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ሀድያ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ ከተማና ወላይታ ድቻ መጫወት የቻለው ይህ አማካይ በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ቆይታ ካደረገ በኋላ ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚመልሰው ዝውውር አጠናቋል።

ሁለተኛው ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ደግሞ የተከላካይ አማካዩ ብርሀኑ አሻሞ ነው። ቀደም ብሎ በደደቢት፣ ወልዋሎ፣ ሲዳማ ቡናና ሀዋሳ ከተማ መጫወት የቻለው ይህ አማካይ ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሶ በሀምበሪቾ መለያ ለመጫወት ተስማምቷል።