ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት 30 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገላቸው

በዶሚኒካን ሪፐብሊክ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ሦስተኛ ዙር ማጣርያ ከኬንያ ጋር በግንቦት ወር ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለደርሶ መልስ ጨዋታዎች ለሚያደርገው ዝግጅት አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል።

በተጨማሪም ጥሪ የተላለፈላቸው ተጫዋቾች ከሚየዚያ 11 ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ በቱሊፕ ኦሊምፒያ ሆቴል በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩም ጥሪ ቀርቧል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች፦

ግብ ጠባቂዎች

አበባየሁ ጣሰው (መቻል)
ሮማን አምባዬ (ቦሌ ክ/ከተማ)
ከንባቴ ከተሌ (ሀምበርቾ)
ፅናት አደፍርስ (ቂርቆስ ክ/ከተማ)

ተከላካዮች

ፀሐይነሽ ጁላ (ሀዋሳ ከተማ)
ሒሩት ተስፋዬ (አዲስ አበባ ከተማ)
ፍቅረአዲስ ገዛኸኝ (ቦሌ ክ/ከተማ)
አሶሬ ሀይሶ (ባህር ዳር ከተማ)
መቅደስ ከበደ (አርባምንጭ ከተማ)
ሰርካለም ሻፊ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ለምለም አስታጥቄ (አርባምንጭ ከተማ)

አማካዮች

ሔለን መንግስቱ (ሀምበርቾ)
ማንአዩሽ ተስፋዬ (ልደታ ክ/ከተማ)
ብርሃን ኃይለሥላሴ (ሀምበርቾ)
ሀና ሲሳይ (አርባምንጭ ከተማ)
ሜሮን አበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ምሌን ጋይም (ቦሌ ክ/ከተማ)
ብዙዓየሁ ፀጋዬ (ቦሌ ክ/ከተማ)
ሜላት ጌታቸው (ቦሌ ክ/ከተማ)

አጥቂዎች

ምትኬ ብርሃኑ (ሲዳማ ቡና)
ሀገሬ ፍትህአለው (ፋሲል ከነማ)
ማህሌት ምትኩ (ሲዳማ ቡና)
ታሪኳ ጴጥሮስ (ሀዋሳ ከተማ)
ቃልኪዳን ጥላሁን (ድሬዳዋ ከተማ)
ዳግማዊት ሰሎሞን (አዲስ አበባ ከተማ)
ቤዛዊት ንጉሤ (ሲዳማ ቡና)
ሳባ ኃይለሚካኤል (አዳማ ከተማ)
ህዳአት ካሱ (ልደታ ክ/ከተማ)
ትዕግስት ወርቄ (ቦሌ ክ/ከተማ)
ዓይናለም ዓለማየሁ (አዲስ አበባ ከተማ)