የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአንድ ተጫዋች ጥሪ አድርጓል

አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ተከላካይ መስመር ላይ አንድ ተጫዋች በጉዳት ምክንያት በማጣታቸው ለተጨማሪ ተጫዋች ጥሪ አድርገዋል።


ከሳምንት በኋላ ለሚደረጉ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ26 ተጫዋች ጥሪ አቅርቦ በዛሬው ዕለት ዝግጁትን የጀመረ ሲሆን መሃል ተከላካይ ቦታ ላይ ጥሪ ደርሶት የነበረው የጣና ሞገዶቹ አምበል ያሬድ ባዬህ በጉዳት ምክንያት ቡድኑን ባለመቀላቀሉ አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ለሲዳማው ጊት ጋትኮች ጥሪ ማቅረባቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።


ብሔራዊ ቡድናችን ግንቦት 29 ከጊኒ ቢሳው ፣ ሰኔ 2 ከጅቡቲ ጋር ጨዋታውን ያከናውናል።