ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታን ይመራሉ

የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን የማጣሪያ መርሐግብር ከቀጣዩ ሳምንት አንስቶ መከናወን ሲጀምር ኢትዮጵያዊያን ሁለት ዳኞች አልጄሪያ ላይ የሚደረግ ጨዋታን ከካሜሮን እና ጅቡቲ አቻቸው ጋር በጣምራ ይዳኛሉ።


በ2026 ለሚደረገው ዓለም ዋንጫ አፍሪካን የሚወክሉ ሀገራትን ለመለየት እንዲረዳ የአፍሪካ ዞን የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከቀጣዩ ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት አንስቶ መደረግ የሚጀምሩ ሲሆን ከሚደረጉ በርካታ ጨዋታዎች መካከል አልጄሪያ በሜዳዋ  ባራኪ በሚገኘው ስታድ ኔልሰን ማንዴላ ስታዲየም ጊኒን ሐሙስ ግንቦት 29 አመሻሽ 10 ሰዓት ላይ ስታስተናግድ ጨዋታውን እንዲመሩ ኢትዮጵያዊያን ሁለት አለም አቀፍ ዳኞች ከካሜሮን እና ጅቡቲ አቻቸው ጋር እንዲዳኙ ተመድበዋል።

ምድብ ስድስትን እየመራች የምትገኘው አልጄሪያ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ ከምትገኘው ጊኒ ጋር የሚያደርጉትን ይህን ጨዋታ በአምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ሲመራ ካሜሮናዊው ኑጉይጉይ ኤልቪስ እና ጅቡቲያዊው አህመድ ሊቨን አብዱራዛቅ ረዳቶቹ ፣ አራተኛ በመሆን ደግሞ ኢትዮጵያዊው ቴዎድሮስ ምትኩ ተሰይሟል። ማሳማ ማሉንጋ በበኩላቸው ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጨዋታውን እንዲታዘቡ ተመርጠዋለ።