የሀሙሱ የዋልያዎቹ ጨዋታ በቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል

ከነገ በስትያ የሚደረገው የጊኒ ቢሳው እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ በቀጥታ ስርጭት የሚታይበት አማራጭ እንዳለ ተገልጿል።

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሦስተኛ ጨዋታ ጊኒ ቢሳው እና ኢትዮጵያ የፊታችን ሀሙስ ወሳኝ ጨዋታ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በቢሳው ከተማ ስታዲዮ 24 ሴቴምብሮ የሚከናወነው ጨዋታ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ይኖረዋል ወይስ አይኖረውም የሚለው ጉዳይ ብዙዎችን ሲያጠያይቅ የቆየ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሠረት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ስታዲየም ለማይገኙ አካላት በበይነ መረብ አማራጭ በቀጥታ ይተላለፋል።

የውድድሩ ባለቤት ፊፋም የራሱ አማራጭ በሆነው ፊፋ+ ሀሙስ ምሽት 1 ሰዓት የሚደረገውን ጨዋታ በቀጥታ እንደሚያሰራጭ ይጠበቃል።