የድሬዳዋ ከተማው ግብ ጠባቂ ለተማሪዎች ድጋፍ አድርጓል

ድሬዳዋ ከተማን በግብ ጠባቂነት እያገለገለ የሚገኘው ዳንኤል ተሾመ በበጎ ልቦች የበጎ አድራጎት ማኅበር ስር ለሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች ድጋፍ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ በሚወዳደረው ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ በግብ ጠባቂነት እያገለገለ የሚገኘው የግብ ዘቡ ዳንኤል ተሾመ በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው እና በወ/ሮ ሰውነት አሸናፊ አማካኝነት ምስረታውን ባደረገው በጎ ልቦች የበጎ አድራጎት ማህበር ውስጥ ወላጅ በማጣታቸው እንዲሁም ደግሞ ቤተሰቦቻቸው አቅመ ደካሞች በመሆናቸው በማህበሩ አማካኝነት ለሚደገፉ 90 ህፃናት ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ማለዳ ላይ የምገባ ድጋፉን አድርጓል።

በተደጋጋሚ በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ድጋፍን ከዚህ ቀደም ሲያደርግ የሚስተዋለው ይህ ግብ ጠባቂ ተማሪዎቹ በቀጣዩ ዓመት የመማሪያ ቁሳቁሶች እንዳይቸግራቸው ለበጎ አድራጎት ማህበሩ ተጨማሪ ድጋፎችንም በቅርብ ቀናት ለማድረግም ቃልን ገብቷል።