ጅማ ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን በበላይነት አጠናቆ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው ጅማ ከተማ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ መሳተፍ ጀምሯል፡፡ ቢንያም ሲራጅ እና አሸናፊ ሽብሩ ደግሞ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ወላይታ ድቻን ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማምራት ያለፉትን ሁለት የውድድር አመታት በቀይ እና ነጭ ለባሾቹ ቤት ያሳለፈው የተከላካይ አማካዩ አሸናፊ ኮንትራቱን ማጠናቀቁን ተከትሎ ለአዲስ አዳጊው ክለብ መፈረሙ ተረጋግጧል፡፡

ቢንያም ሲራጅ በሐረር ቢራ (ሐረር ሲቲ) እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለረጅም አመታት የመጫወት ልምድ ያለው የመሀል ተከላካይ ሲሆን ከፕሪምየር ሊጉ የወረደው ንግድ ባንክን ለቆ ለጅማ ከተማ ፊርማውን አኑሯል፡፡

ጅማ ከተማ በቀጣዩ የውድድር አመት በሊጉ ለመደላደል በማሰብ በርካታ የሊጉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ሲገኝ የአዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውር በቀጣይ ቀናት ይፋ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

3 thoughts on “ጅማ ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

 • July 22, 2017 at 7:03 pm
  Permalink

  የአሠልጣኝ ገ/መድህንን ለጅማ ከተማ መፈረም ለምን አልዘገባችሁም??

  • July 26, 2017 at 10:46 am
   Permalink

   ጂማዎች እባካችሁ የቀድሞ የወላይታ ዲቻ እና የወልዲያ ከነማ ተጫዋች የነበረውን ጠንካራውንና በጣም ጎበዝ የሆነውን በሱፐር ሊጉ አለ የሚባለውን ጠንካራውን የተከላካይ መሥመር ተጫዋች አስቻለው ዘውዴን ተመልከቱት የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቢያንሥ እንኳን ሙከራ እንዲያደርግ ብትጋብዙት፤ ተጫዋቹን ቢመለከቱት በጣም ጠንካራ ሥለሆነ አደራችሁን ብታዩት በጣም ምርጥ የተባለ የተከላካይ መሥመር ተጫዋች ነው፡፡

Leave a Reply

error: