ቻምፒየንስ ሊግ | ወደ ምድብ ያለፉት 16 ቡድኖች ታውቀዋል

በካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ ወደ ምድብ ለመግባት የተደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ በተደረጉ ጨዋታዎች ተጠናቋል፡፡ 16 አላፊ ክለቦች በታወቁባቸው ጨዋታዎች ያልተጠበቁ ቡድኖች ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ቻምፒየንስ ሊጉ ምድብ ድልድል መግባት የቻሉባቸው ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

ለወትሮም ቢሆን ወደ ምድብ ድልድል መግባት ሲቸግራቸው የማይታዩት እንደኤኤስ ቪታ እና አል ሂላል ያሉ ክለቦች ባልተጠበቀ መልኩ ሲሸነፉ ኬሲሲኤ፣ ታውንሺፕ ሮለርስ፣ ኤኤስ ፖርት ቶጎ እና ምባባኔ ስዋሎስ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ምድብ ማለፍ ችለዋል፡፡ ደካማ የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኘው የኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ በዩጋንዳው ኬሲሲኤ በአጠቃላይ ውጤት 1-0 ተሸንፎ ወደ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ምድብ ለማለፍ ለሚደረገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ወርዷል፡፡ የወቅቱ ቻምፒዮን ዋይዳድ ካዛብላንካ እና የፍፃሜ ተፋላሚ የነበረው አል አህሊ እምብዛም ሳይቸገሩ ምድቡን የተቃቀሉ ሲሆን ቲፒ ማዜምቤ ቤይራ ላይ ያልተጠበቀ የ3-0 ሽንፈትን ቢቀምስም ከሁለት የውድድር ዘመናት ቆይታ በኃላ ወደ ቻምፒየንስ ሊጉ ምድብ ተመልሷል፡፡

የተመዘገቡ ውጤቶች

(በቅንፍ የተጠቀሱት የአጠቃላይ ውጤቶች ናቸው)

ካምፓላ ሲቲ ኮውንስል ኦቶዎሪቲ (ዩጋንዳ) 1-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ) (1-0)
ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ) 1-0 ዛናኮ (ዛምቢያ) (3-1)
ዊልያምስቪል (ኮትዲቯር) 2-0 ዋይዳድ ክለብ አትሌቲክ (ሞሮኮ) (4-7)
ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን) 1-3 አል አህሊ (ግብፅ) (1-7)
ሞውሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) 6-0 ማውንቴን ኦፍ ፋየር ሚኒስትሪ (ናይጄሪያ) (7-2)
ጄኔሬሽን ፉት (ሴኔጋል) 0-2 ሆሮያ አትሌቲክ ክለብ (ጊኒ) (1-4)
ታውንሺፕ ሮለርስ (ቦትስዋና) 0-0 ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) (2-1)
ሶንጎ (ሞዛምቢክ) 3-0 ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) (3-4)
ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) 1-0 ፕሪሜሪ አውጉስቶ (አንጎላ) (1-1) (ፕሪሜሮ በመለያ ምት 3-2 አሸንፏል)
ኢኤስ ሴቲፍ (አልጄሪያ) 4-0 አዱና ስታርስ (ጋና) (4-1)
ኤስፔራንስ ስፖርቲቭ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) 1-0 ጎር ማሂያ (ኬንያ) (1-0)
ፕሌቶ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) 1-0 ኤትዋል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ)(3-4)
አል ሂላል ኦምዱሩማን (ሱዳን) 3-1 ኤኤስ ፖርት ቶጎ (ኮትዲቯር) (3-3) (ፖርት ቶጎ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ግብ አልፏል)
አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር) 1-2 ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) (2-2) (ዜስኮ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ግብ አልፏል)
ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 2-2 ዲፋ ኤል ጃዲዳ (ሞሮኮ) (2-3)
ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) 2-0 ራዮን ስፖርትስ (ሩዋንዳ) (2-0)


ወደ ምድብ ያለፉ ክለቦች

ኬሲሲኤ (ዩጋንዳ) ፣ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ) ፣ አል አህሊ (ግብፅ) ፣ ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ) ፣ ሞውሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) ፣ ሆሮያ አትሌቲክ ክለብ (ጊኒ) ፣ ታውንሺፕ ሮለርስ (ቦትስዋና) ፣ ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ፣ ፕሪሜሪ አውጉስቶ (አንጎላ) ፣ ኢኤስ ሴቲፍ (አልጄሪ) ፣ ኤስፔራንስ ስፖርቲቭ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) ፣ ኤትዋል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ) ፣ ኤኤስ ፖርት ቶጎ (ቶጎ) ፣ ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) ፣ ዲፋ ኤል ጃዲዳ (ሞሮኮ) ፣ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *