ኮንፌድሬሽን ዋንጫ | የክለብ አፍሪካ እና ዛማሌክ ከውድድር መውጣት ብዙዎችን አስገርሟል

በቶታል ካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎች ከአርብ ጀምሮ ተደርገዋል፡፡ ያልተጠበቁ ውጤቶች በሁለተኛው የአፍሪካ የክለቦች ውድድር ላይም ሲመዘገቡ የሰሜን አፍሪካ ሃያሎቹ ዛማሌክ እና ክለብ አፍሪካ ከውድድር መውጣታቸው የሳምንቱ መነጋገሪ ሆኗል፡፡

የአምስት ጊዜ የአፍሪካ ቻምፒዮኑ ዛማሌክ በኢትዮጵያው ወላይታ ድቻ በመለያ ምቶች 4-3 ሲሸነፍ በጥሩ ግስጋሴ ላይ የተገኘው የሞሮኮው በርካን ሳይጠበቅ ክለብ አፍሪካን በልማደኛው አጥቂ አዩብ ኤል ካቢ ጎል ቱኒዝ ላይ 1-0 አሸንፎ አልፏል፡፡ አል አሃሊ ሸንዲ በኮንጎ ብራዛቪሉ ላ ማንቻ ተሸንፎ ከውድድሩ ሲሰናበት አል መስሪ፣ ራጃ ካዛብላንካ፣ ኢንየምባ፣ ፎሳ ጁኒየርስ፣ ዩኤስኤም አልጀር እና አክዋ ዩናይትድ ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉ ክለቦች ናቸው፡፡ የአምናው የፍፃሜ ተፋላሚ ሱፐርስፖርት ዩናይትድም በፔትሮ አትሊቲኮን አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡

በሁለተኛው እና የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ከቻምፒየንስ ሊጉ የወረዱ 16 ክለቦች አሁን ወደ ሁለተኛው ዙር ካለፉት ጋር ተደባልቀው የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያርጋሉ፡፡ የሚልፉ 16 ቡድኖች ወደ ምድብ የሚገቡ ይሆናል፡፡ በመጪው ረቡ በውድድሩ ላይ የሚሳተፉት ወላይታ ድቻ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን የሚያውቁ ይሆናል፡፡ ድቻ ከቻምፒየንስ ሊጉ ከወረደ ክለብ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚፋለምበት እድል ሊደረሰው ይችላል፡፡

የተመዘገቡ ውጤቶች

(በቅንፍ የተጠቀሱት የአጠቃላይ ውጤት ነው)

ዛማሌከ (ግብፅ) 2-1 ወላይታ ድቻ (ኢትዮጵያ) (3-3) (ወላይታ ድቻ በመለያ ምት 4-3 አሸንፏል)
ሱፐርስፖርት ዩናይትድ (ደቡብ አፍሪካ) 2-1 ፔትሮ አትሌቲኮ (አንጎላ) (2-1)
አል አሃሊ ሸንዲ (ሱዳን) 2-1 ላ ማንቻ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) (2-4)
አርሚ ፒፕልስ ሬዚስታንስ (ሩዋንዳ) 2-1 ጆሊባ ኤሲ (ማሊ) (2-2) (ጆሊባ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ግብ አልፏል)
አል ሂላል ኦብዬድ (ሱዳን) 6-0 ኦሎምፒክ ስታር (ብሩንዲ) (6-0)
ናካና (ዛምቢያ) 1-0 ሲአር ቤሎዝዳድ (አልጄሪያ) (1-3)
አል መስሪ (ግብፅ) 0-0 ሲምባ (ታንዛኒያ) (2-2) (መስሪ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠራቸው ግቦች አሸንፏል)
ክለብ አፍሪካ (ቱኒዚያ) 0-1 ሬኔሳንስ በርካን (ሞሮኮ) (1-4)
ኖዲቦህ (ሞሪታንያ) 2-4 ራጃ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ) (3-5)
ኬፕ ታውን ሲቲ (ደቡብ አፍሪካ) 1-2 ኮስታ ዶ ሶል (ሞዛምቢክ) (2-2) (ኮስታ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠራቸው ግቦች አልፏል)
ኢንየምባ (ናይጄሪያ) 3-2 ኢነርጂ (ቤኒን) (5-2)
ፎሳ ጁኒየርስ (ማዳጋስካር) 1-0 ፖር ሉዊ (ሞሪሺየስ) (3-0)
ዩኒየን ስፖርቲቭ መዲና ደ አልጀር (አልጄሪያ) 1-1 ማኒማ ዩኒየን (ዲ.ሪ. ኮንጎ) (3-3) (ዩኤስኤም አልጀር ከሜዳው ውጪ ባስቆጠራቸው ግቦች አልፏል)
ዲፖርቲቮ ኒፋግ (ኤኳቶሪያል ጊኒ) 1-0 ሞቴማ ፔምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) (2-1)
አክዋ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) 1-0 አል ኢቲሃድ ትሪፖሊ (ሊቢያ) (1-1) (አክዋ በመለያ ምቶች 3-2)
ቤን ጉርደን (ቱኒዚያ) 3-1 ካራ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) (3-4)

ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉ ክለቦች

(ከቻምፒየንስ ሊጉ የወረዱትንም ይጨምራል)

ወላይታ ድቻ (ኢትዮጵያ)፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ)፣ አል ሂላል (ሱዳን)፣ አል ሂላል ኦብዬድ (ሱዳን)፣ ላ ማንቻ (ኮንጎ ሪፐብሊክ)፣ ካራ ብራዛቪል (ኮንጎ ሪፐብሊክ)፣ ራጃ ክለብ አትሌቲክ (ሞሮኮ)፣ ሬኔሳንስ በርካን (ሞሮኮ)፣ ጆሊባ (ማሊ)፣ ቤሎዚዳድ (አልጄሪያ)፣ አል መስሪ (ግብፅ)፣ ኮስታ ዶ ሶል (ሞዛምቢክ)፣ ኢኒየምባ (ናይጄሪያ)፣ አክዋ ዩናይትድ (ናይጄሪያ)፣ ማውንቴን ኦፍ ፋየር ሚኒስትሪ (ናይጄሪያ)፣ ፕሌቶ ዩናይትድ (ናይጄሪያ)፣ ፎሳ ጁኒየርስ (ማዳጋስካር)፣ ዩኤስኤም አልጀር (አልጄሪያ)፣ ዲፖርቲቮ ኒፋግ (ኤኳቶሪያ ጊኒ)፣ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ (ደቡብ አፍሪካ)፣ ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ)፣ ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ)፣ ዛናኮ (ዛምቢያ)፣ አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር)፣ ዊልያምስቪል (ኮትዲቯር)፣ ጎር ማሂያ (ኬንያ)፣ ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን)፣ ሶንጎ (ሞዛምቢክ)፣ አዱና ስታርስ (ጋና)፣ ጄኔሬሽን ፉት (ሴኔጋል)፣ ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)፣ ራዮን ስፖርትስ (ሩዋንዳ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *