ፋሲል ከተማ ሰለሞን ሀብቴን አስፈረመ

በዝውውር መስኮቱ ፍጥነቱን ጨምሮ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ፋሲል ሰለሞን ሀብቴን የግሉ አድርጓል።

የግራ መስመር ተከላካይ እና የአማካይ ስፍራ ላይ መጫወት የሚችለው ሰለሞን ደደቢትን ለቆ በ2008 ወደ ወላይታ ድቻ ካመራ ከአንድ ዓመት በኋላ በድጋሚ ወደ ደደቢት ተመልሶ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት አሳልፏል። አሁን ደግሞ ወደ ፋሲል በሁለት ዓመት ኮንትራት ማምራቱ ታውቋል። በቦታውም ከአምሳሉ ጥላሁን ከባድ ፉክክር እንደሚገጥመው ይጠበቃል።

በዝውውር መስኮቱ ከየትኛውም ክለብ በበለጠ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ፋሲል ከሰለሞን በተጨማሪ በዛብህ መለዮ፣ ሐብታሙ ተከስተ፣ ሽመክት ጉግሳ እና ከድር ኩሊባሊን አስፈርሟል።