ደቡብ ፖሊስ ሳዲቅ ሴቾን ሲያስፈርም የሁለት ተጫዋቾች ውል አድሷል

ወደ ፕሪምየር ሊጉ መመለሱን ካረጋገጠ በኋላ በዝውውር መስኮቱ በስፋት እየተሳተፈ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ሳዲቅ ሴቾች አስፈርሟል። የሁለት ተጫዋቾችንም ውል አድሷል።

የቀድሞው የሼር ኢትዮጵያ አጥቂ ከሁለት ዓመት የኢትዮጵያ ቡና ቆይታ በኋላ በአምናው የውድድር ዓመት ወደ ሀዋሳ ከተማ ቢያመራም ብዙም የመጫወት እድል ሳያገኝ በውድድር ዓመቱ ክለቡን በመልቀቅ ለስድስት ወራት ክለብ አልባ ሆኖ ቆይቶ ወደ ሌላው የሀዋሳ ክለብ ደቡብ ፖሊስ አምርቷል። በመስመር እና የመሀል አጥቂነት የሚሰለፈው ሳዲቅ ደቡብ ፖሊስን በአንድ የውድድር ዓመት ውል ነው የተቀላቀለው።

ከአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ጋር ከተለያየ በኋላ ዘላለም ሽፈራውን አሰልጣኝ አድርጎ የቀጠረው ደቡበ ፖሊስ  ከአዳዲስ ተጫዋቾች ጎን ለጎን የነባሮችን ውል እያደሰ ይገኛል። አምበሉ ቢንያም አድማሱ እና የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ደስታ ጊቻሞ ውላቸውን ለተጨማሪ አንድ ዓመት ያደሱ ተጫዋቾች ናቸው።