ዳንኤል አጄይ የጅማ አባ ጅፋር ውሉን አራዝሟል

የፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮን የወሳኝ ግብ ጠባቂው ዳንኤል አጄይን ኮንትራት ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ማራዘሙን አስታውቋል፡፡
ጋናዊው ግብ ጠባቂ ባለፈው የውድድር ዓመት በግል ጉዳይ ወደ ሆላንድ አምርቶ በዛው መቆየቱን ተከትሎ የክለቡ ቆይታ ጠራጣሪ ሆኖ የነበረ ቢሆንም ተመልሶ በመምጣት ለክለቡ ውጤታማነት ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ በክረምቱ በርካታ ተጫዋቾችን የለቀቀው ጅማ ዳንኤል አጄይን ውል ለማራዘም ከዚህ ቀደም ከስምምነት ደርሶ የነበረ ቢሆንም ተጫዋቹ ከእረፍት ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ከትላንት በስቲያ በመሆኑ ዛሬ ፊርማውን በማኖር ውሉን አራዝሟል፡፡

ጅማ አባ ጅፋር አዲስ ያስፈረመው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ዘሪሁን ታደለ እና ሚኪያስ ጌቱን በመያዝ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡