ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ ሰባት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እየደረሰ በተደጋጋሚ የሚመለሰው ሀላባ ከተማ ዘንድሮም ወዳሰበበት ሊግ ለመቀላቀል በተጫዋቾች ዝውውር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾችንም ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በአሰልጣኝ ሚሊዮን አካሉ የሚመራው ሀላባ ከተማ በፊት መስመር ወሳኝ የነበሩት እንደ ተመስገን ይልማ እና ስንታየው መንግስቱን ጨምሮ አስቻለው ኡታ፣ መሀመድ ናስር፣ አበባው አመኑ እና አብነት ተሾመን ክለቡ ያጣ ሲሆን በምትካቸው ደግሞ ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ አምጥቷል። በዚህም መሰረት ምትኩ ማመጫ (አማካይ ከዲላ ከተማ)፣ ኤፍሬም ቶማስ (አጥቂ ቡታጅራ)፣ አቡበከር ወንድሙ (አጥቂ ካፋ ቡና)፣ ታጅር ጃፋር (አጥቂ ናሽናል ሲሜንት)፣ ሙሉቀን አዲሱ (ተከላካይ ከቡታጅራ)፣ ክብረአብ ፍሬው (አማካይ ነቀምት) እና ዘሪሁን ይልማ (አማካይ ከቡታጅራ ከተማ) ፈርመዋል፡፡

ክለቡ  ራሱን ለማጠናከር በቀጣይ ቀናት አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ክለቡ ለማምጣት ማቀዱን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡