ደደቢት ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

ሁነኛ የአጥቂ ክፍል ተሰላፊን ለማስፈረም በርከት ላሉ ተጫዋቾች የሙከራ ዕድል ሰጥተው የነበሩት ሰማያዊዎቹ ጋናዊው አጥቂ ሻምሱ አልሃሰንን አስፈርመዋል።

ቶጓዊው አጥቂ ኤደም ሆሮሶውቪን ጨምሮ በርከት ላሉ የአጥቂ ክፍል ተሰላፊዎች የሙከራ ዕድል ሰጥተው የነበሩት ደደቢቶች የ25 ዓመቱ ጋናዊ አጥቂ ሸምሱ አልሃሰንን ከቦኸም ዩናይትድ አስፈርመዋል። በትላንትናው ዕለት ሁለት የአጥቂ ክፍል ተሰላፊዎች አሌክሳንደር ዓወት እና ሙሉጌታ ብርሃነን ያስፈረሙት ደደቢቶች የሻምሱ ዝውውር በአጥቂ መስመር ላይ አማራጭ ያሰፋላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሻምሱ አልሃሰን ከዚህ በፊት ለኢንተር አላይስ ፣ ቦኸም ዩናይትድ እና ፒዩር ጆይ የተጫወተ ሲሆን ለደደቢት ከግብ ጠባቂው ረሺድ ማታውሲ እና ክዌክ ኢንዶህ ቀጥሎ በዘንድሮው ዓመት የሚጫወተው ሶስተኛው የውጪ ሃገር ዜጋ ሆኖ ተመዝግቧል።


ማስታወቂያ
የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የዋናው እግርኳስ ቡድን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች የቪድዮ ቀረጻ እና የጨዋታ ትንተና የሚያደርግ ባለሙያ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩ አካላት በስራው ላይ ያላቸውን የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ በመያዝ ሜክሲኮ በሚገኘው የክለቡ ጽህፈት ቤት በአካል በመቅረብ የፍላጎት ማሳወቂያ እና የመወዳደርያ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ – 0115-534949 ; 0115-532051

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ