ወልዋሎ ፌዴሬሽኑን ካሳ ጠየቀ

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቅዳሜ ሊያደርገው የነበረው ጨዋታ በመራዘሙ ለተጨማሪ ወጪ በመዳረጉን በመግለፅ የካሳ ክፍያ እንዲከፈለው ጠየቀ።

በአምስትኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ቅዳሜ ሊካሄድ የነበረው የመከላከያ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ የአዲስ አበባ ስታድየም ዓመታዊው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል እንደሚከበርበት በመግለፅ ወደ ሰኞ 11:00 መዘዋወሩን ተከትሎ  እንግዳው ቡድን ወልዋሎ ለተጨማሪ ወጪዎች መዳረጉን አስታውቋል። ጨዋታው በመራዘሙ ምክንያት ክለቡ ከእቅድ ውጪ ያወጣውን ወጪም ፌዴሬሽኑ እንዲሸፍን ከታች ባለው ደብዳቤ ጠይቋል።