ኮሚሽነር ሸረፋ ዴሌቾ ይግባኝ ጠየቁ

የፌዴሬሽኑ ብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ደንብና አሰራርን መሠረት ያላደረገ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፎብኛል በማለት በዕለቱ የበረውን ሁኔታ የሚገልፅ ቴክኒካል ምላሽ የያዘ ሰነድ አባሪ በማድረግ የይግባኝ ደብዳቤ አስገቡ።

በመቐለ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ጥር 30 መቐለ 70 እንድርታ ከፋሲል ከነማ ባደረጉት ጨዋታ የውድድሩ ኮሚሽነር ሆነው የተመደቡት ሸረፋ ዴሌቾ በተመደቡበት ጨዋታ ላይ የደንብ ስህተት ፈፅመዋል በማለት ነገሮችን በጥልቀት እና ስፋት በዝርዝር ከመረመረ በኋላ ኮሚሽነሩ ጨዋታው ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ3 ወራት ከውድድሮች እንዲርቁ የቅጣት ውሳኔ ትላንት ማስተላለፉ ይታወቃል።

ኮሚሽነር ሸረፋ ዴሎቾ የዳኞች ብሔራዊ ኮሚቴ የወሰነብኝ የዲሲፒሊን ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ዛሬ ለፌዴሬሽኑ ይግባኝ ደብዳቤ አስገብተዋል። ኮሚሽነር ሸረፋ ለተወሰነባቸው ውሳኔ ምላሽ የሚሆን ቴክኒካል ዝዝርር ነገሮችን በደብዳቤያቸው ያካተቱ ሲሆን በዋናነት “የዳኞች ብሔራዊ ኮሚቴ የመቅጣት ስልጣን የለውም፤ ውሳኔው ደንብና አሰራርን መሠረት ያደረገ አይደለም። በእስከዛሬው የዳኝነትም ሆነ የኮሚሽነር ስራዬ እኔን የማይገልፅ ስም የማጥፋት ዘመቻ ተደርጓል። ” በማለት ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ
በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *