የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ የዝውውር መረጃዎች

የከፍተኛ ሊግ ግማሽ ዓመት የዝውውር መስኮት ላይ ክለቦች ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። በምድብ ሀ የሚገኙ ክለቦች ያደረጓቸው የዝውውር እንቅስቃሴዎች በከፊል እነዚህን ይመስላሉ

– ምድብ ሀ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ለገጣፎ ለገዳዲ የፊት መስመር ተጫዋች የሆነውና አምና በመቂ ከተማ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው በላይ ያዴሳን ከኢኮስኮ አስፈርሟል።

– በዘንድሮ ውድድር ዓመት ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደገው አቃቂ ቃሊቲ በስብስብ ላይ ሁለት ተጫዋቾች ጨምሯል። ጌትነት ታፈሰ ከፌደራል ፖሊስ እና ዮናስ ባቤና ከአራዳ ክ/ከተማ የፈረሙ አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው። ዮናስ ባቤና በመጀመርያ የቡድኑ ጨዋታው ወልዲያ ላይ ጎል አስቆጥሮ ለቡድኑ አንድ ነጥብ ማስገኘትም ችሏል።

– ወልዲያ የአጥቂ ስፍራውን ለማጠናከር ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል። ወጣቱ አቤል ከበደ እና አንጋፋው አሸናፊ አደም የክለቡ አዳዲስ ፈራሚዎች ናቸው።

– ሁለተኛውን ዙር ቡራዩን 2-0 በማሸነፍ የጀመረው ደሴ ከተማ አራት ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። በከፍተኛ ሊጉ የመጫወት ልምድ ያለው አጥቂው ሊቁ አልታዬን ከጅማ አባቡና፣ የቀድሞ የወልዲያ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች በድሩ ኑርሁሴን ከአዲስ አበባ ከተማ፣ በንግድ ባንክ እና ሙገር እና ሐረር ቢራ ተጫውቶ ያሳለፈው ተከላካዩ አቤል አበበ ከአዉስኮድ እንዲሁም አማካዩ ዓለማየሁ ማሞ ከደቡብ ፖሊስ ለክለቡ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው። በድሩ ኑርሁሴን ቡድኑ ቡራዩን 2-0 ሲያሸንፍ ሁለቱንም ጎሎች ማስቆጠሩ ይታወሳል።

– በሻምበል መላኩ የሚመራው ወሎ ኮምቦልቻ በግማሽ ዓመቱ ስድስት ተጫዋች ወደ ቡድኑ ሲቀላቀል ሁለት ታዳጊዎች ወደ ዋናው ቡድን አሳድጓል። ስለሺ ዘሪሁን (አክሱም ከተማ)፣ አቤል አስፋው (አውስኮድ)፣ አትክልት ንጉሴ (ደሴ ከተማ)፣ መሐመድ አብደላ (ደቡብ ፖሊስ) አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ሲሆኑ ግሩም ሀጎስ እና ፋሲል አየለ ወደ ዋናው ቡድን ያደጉ ተጫዋቾች ናቸው።

– አዲስ አዳጊው ገላን ከተማ ሰዒድ ሀሰንን ከአክሱም ከተማ ወደ ቡድኑ መቀላቀል ችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *