የአንደኛ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር የዛሬ ጨዋታዎች ወደ ነገ ተዘዋውረዋል

ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚገቡ ስድስት ቡድኖች ተለይተው የሚታወቁበት የማጠቃለያ ውድድር በባቱ ከተማ (ዝዋይ) ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም የምድብ ሀ እና ለ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ ተብሎ መርሐ ግብር ቢወጣላቸውም በባቱ ዛሬ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ሳይከናወኑ ቀርተዋል።

በዚህም መሠረት ጨዋታዎቹ ወደ ነገ መዞራቸው ታውቋል።

ማክሰኞ ሐምሌ 16 ቀን 2011

03:00 | ኮልፌ ቀራንዮ ከ ላስታ ላሊበላ (ባቱ ሜዳ)
03:00 | ጎፋ ባሬንቼ ከ አዲስ አበባ ፖሊስ (ሼር ሜዳ)
05:00 | መቱ ከተማ ከ ዳሞት ከተማ (ሼር ሜዳ)
05:00 | ጋሞ ጨንቻ ከ ራያ አዘቦ (ባቱ ሜዳ)

የምድብ ሐ እና መ ትላንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ባቱ ከተማ፣ ሱሉልታ ከተማ፣ ሰሜንሸዋ ደብረብርሀን እና ሰሎዳ ዓድዋ ወደ ሩብ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ አስቀድሞ ማለፉን ያረጋገጠው ቂርቆስ ክ/ከተማን ተከትለው የሚያልፉ ሌሎች ሦስት ቡድኖች የሚለዩ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡