የትግራይ ዋንጫ ዕጣ ማውጣት ስነ ሥርዓት ሲካሄድ ወልዋሎ በውድድሩ እንደሚሳተፍ ተገልጿል

በሸቶ ሚድያ ኮሚኒኬሽን፣ የትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የትግራይ ስፖርት እና ወጣቶች ፅህፈት ቤት በጋራ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው የትግራይ ዋንጫ ዛሬ በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱ ተካሂዷል።

ከዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት በፊት ወልዋሎ በውድድሩ እንደሚሳተፍ ሲገለፅ ውድድሩም ከሁለት ቀናት በኃላ መቐለ 70 እንደርታ እና ወላይታ ድቻ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል። ከዚህ በተጨማሪ የውድድሩ የትኬት ዋጋ 50 ብር እና 30 ብር ሲሆን በእያንዳንዱ ጨዋታ ኮከብ ተብሎ ለሚሸለምም ዲኮደር እንዲሁም ለውድድሩ ሽልማት እስከ 200ሺህ የሚደርስ ሽልማት ይሰጣል ተብሏል።

በተያያዘ ዜና ወልዋሎዎች በትግራይ ዋንጫ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል። ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ዋንጫ ይሳተፋሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ወልዋሎዎች በትግራይ ዋንጫ እንደሚሳተፉ አቶ አንገሶም ካሕሳይ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

ምድብ አንድ          ምድብ ሁለት

1) መቐለ              1) ወልዋሎ
2) ወላይታ ድቻ      2) ሲዳማ ቡና
3) ደደቢት             3) ስሑል ሽረ
4) አክሱም ከተማ  4) ሶሎዳ ዓድዋ

እሁድ ጥቅምት 30

8:00| መቐለ ከ ወላይታ ድቻ
9:30| ደደቢት ከ አክሱም


© ሶከር ኢትዮጵያ