ድሬዳዋ ከተማ የቅሬታ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ አስገባ

ድሬዳዋ ከተማ በስምንተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቅዱስ ጊዮርጊስ የ3ለ2 ሽንፈት ካስተናገደበት ጨዋታ በኋላ “በደል ደርሶብናል” በማለት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የቅሬታ ደብዳቤን አስገብቷል፡፡

ክለቡ በደብዳቤው ” ቡድናችን ከጨዋታው በኋላ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች የድብደባ እና ስድብ በደል ፈፅመውብናል፡፡ የካሜራችን ምስል እንዲጠፋ ተደርጎብናል፤ የአመራሮቻችንም ስልክ ተነጥቆ በውስጡ የነበረው መረጃ እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡ የፀጥታ አካላት ሊተባበሩን አልቻሉም። ስለሆነው ፌዴሬሽኑ ተገቢውን መልስ ይስጠን” የሚል ይዘት ያለው ቅሬታ ነው ለፌዴሬሽኑ ያስገባው፡፡

ክለቡ ያስገባው ደብዳቤ 👇


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: