ሶከር ታክቲክ | መጠቅጠቅ – ጥግግት (Compactness)

አሰልጣኝ ደስታ ታደሰ ከተለያዩ ድረ-ገጾች ያገኛቸውን የእግርኳስ ታክቲክ ንድፈ-ሐሳቦችን የተመለከቱ ጥልቅ ትንተናዎች፣ የሥልጠና መመሪያዎች እና መጻህፍትን ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ በመተርጎም ሌሎች አሰልጣኞችና አንባቢን ይጠቅም ዘንድ ጥቅም ላይ ለማዋል ይሞክራል፡፡ ከዚህ በታች የቀረበው ፅሁፍም አንዱ አካል ነው፡፡


“መከላከል ምንድነው? መከላከል-ምን ያህል ቦታ መከላከል እችላለሁ? ስለሚለው ነው፡፡ሁሉ ነገር ስለ ሜትር ነው፣ይህ ብቻ ነው” ጆን ክሯይፍ

መከላከልና መጠቅጠቅን መለካት

በእግርኳስ  የመጠቅጠቅ ተቀራራቢ ትርጉም በሜዳ ላይ ተራርቀው በሚገኙ ተጫዋቾች መካከል በአግድሞሽና በቁመት አጭር ርቀትን ጠብቆ መቆየት ነው፡፡ ነገር ግን በአተገባበሩ ላይ መሰረታዊ ምላሽ የመስጠት እጥረት ይታያል፡፡ ሲጀመር የመጠቅጠቅ ትክክለኛ ደረጃ የቱ ነው? ለዚህ የተሻለ ቀላል ትርጉም የሚሰጥና ተግባራዊነቱ የተረጋገጠ ትርጉም እንደሚኖር እመኑ፡፡

መሰረታዊ ሃሳቡ  ቀዮቹ በቁመትና በጎን ትልቅ ርቀት አላቸው ይህም እንዳይጠቀጠቁ አድርጓቸዋል ፡፡

እንደ  አማራጭ በግል ደረጃ መዘርዘርም ይቻላል፡፡የቡድን ቅርፅእንደተጠበቀ ሆኖ መጠጋጋትን ለማረጋገጥ በቅርብ ርቀት በበቂ ሁኔታ መጠጋጋት የሚያስችል ሁኔታን መፍጠር ይቻላል ፡፡ይህ ዋናው ጉዳይ ነው፡፡በዚህ ነጥብ ላይ ነው የመጠቅጠቅ አስተዋጽኦ  በዋነኝነት  የሚቀርበው ይህም የቃሉ ተመራጭ ትርጉም እና ልኬት ያደርገዋል፡፡ነገር ግን 10 ተጫዋቾች በ የ 5 ሜትር ርቀት ቆመውም የመከላከል ጥንካሬው ደካማ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ጥሩ የመጠቅጠቅ ደረጃ የቱ ነው? ይህ በተቃራኒ ቡድን ላይ ጥገኛ ሊሆን ይችላል፡፡ይሁን እንጂ  መነሻ ነጥብ ሊሆን የሚችለው ተጫዋቾች መቀራረባቸውን እንደጠበቁ በተቻለ መጠን ተራርቀው የሚቆሙበት ቦታ ነው፡፡የመጠቅጠቅ ጥቅምን በመጠበቅ ብዙ ቦታም መሸፈን ይችላል ፡፡

ሌላኛው መከራከሪያ ደግሞ መጠቅጠቅ ከተቃራኒ ቡድን አቋቋም አንፃር መሆን አለበት የሚለው ነወ፡፡ቡድኑ በራሱ ያለው መጠቅጠቅ ብቻ ሳይሆን በቡድኑ እና በተቃራኒ ቡድን መካከል ያለው ርቀት አጭር መሆን ነው፡፡በዚህም ቁልፍ የመጠቅጠቅ መርኸ ይሳካል፡፡ተቃራኒ ቡድን የሚጫወትበት ቦታ ይቀንሳል፡፡

      መጠቅጠቅ የመከላካል ጥቅም

1 የመከላከል መስተጋብር (defensive connection)

ከፍተኛ የመጠቅጠቅ ደረጃ ላይ የሚደረሰው በተከላካዮቹ መካከል ከመጠን በላይ የሰመረ ግንኙነት ሲኖር ነው፡፡በተጫዋቾች መካከል የሚፈጠር ግንኙነት (connection) በቅርብ ርቀት ያለ ተጫዋቾች የቡድን አጋራቸውን ለማገዝ ወይም ሁለተኛ ፕረስ አድራጊ ሆነው ሲገኙ ባላቸው አቋቋም ሊገለፅ ይችላል፡፡ይህ የመከላከል አደረጃጀት በቁጥር ልቀውና ወደ ውስጥ ዘልቀው ሊገቡ የሚሞክሩ ተቃራኒ ቡድኖችን ለመከላከል አስተማማኝ ይሆናል፡፡

በተጫዋቾች መካከል የሚኖር አጭር ርቀት ኳስ የማሰራጫ መስመሮችን ስለሚቀንስ ወደ  ተጋጣሚ ቡድን ዘልቆ የሚገባ ኳስ ለማቀበል አዳጋች ይሆናል፡፡

 

ባልተጠቀጠቀ መከላከል የሚታይ የመከላከል ግንኙነት

ከላይ እንደቀረበው ያልተጠቀጠቀ ቅርፅ ባለው መከላከል የመሀል ተጨዋቹ በሆነ መንገድ ኳስ በያዘው ተጫዋች ቢጠቃ 2 ተጫዋቾቸ ብቻ አጠገቡ አሉ፡፡ በጊዜ ደርሰው ለማገዝ ሌሎች 3 ተጫዋቾች የሚገኙት በርቀት ነው፡፡በዚህ ጉዳይ የባሰው ነገር ሰው በሰው መያዝንም ስላላወቁ ሁለቱ የተነጠሉ ተጫዋቾች መሃሉ እንዳይከፈት መጠበቅ አለባቸው ፡፡በቢጫው ከደመቀው ቦታ በመነጠላቸው መሃል መዋቅሩ(structure) በጣም ደካማና በቀላሉ ሊከፈት የሚችል ሆኗል፡፡

 

በተጠቀጠቀ መከላከል የተሻለ ግንኙነት አስፈላጊ ነው ፡፡

በንፅፅር፡-ተጫዋቾች በጥሩ መጠቅጠቅ ከተደራጀ ቡድን ጋር ሲሆን ከሌሎች አምስት ተጫዋቾች ጋር ግንኙነት ይኖረዋል፤ሶሥቱ ከመሀል ክፍል ቁልፍ በሆነው የሜዳ ክፍል ላይ የመከላከል መረጋጋትን ይፈጥራሉ፡፡ከዚህ ውጪ ቡድኑ ኳስ ባለበት ቦታ ላይ ተጨማሪ ሁለቱ  ፕረሲንጉን የሚያግዙ ተጫዋቾች መኖራቸው ቡድኑ ትርፍ እንዲያገኝ ያደርገዋል፡፡

2 የተሻለ የመከላከል መዳረሻ (improved defensive access)

የተጠቀጠቀ የመከላካል አዘጋግ ለኳሱ የተሻለ የመከላከል መዳረሻ (access) መጠቀም ያስችላል፡፡ የሚከላከለው ቡድን በሆነ መንገድ ኳስን ለመንጠቅ ትክክለኛና ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ፕረስ እንዲደርጉ ያስችላቸዋል ፡፡

 

ፕረስ ሲያደርግ ደካማ መዳረሻ ያለው ቡድን

 

  • የሚከላከለው ቡድን ለኳሱ ደካማ የሆነ መዳረሻ ይዟል፡፡
  • በዚህም በትክክል ፕረስ ማድረግ አይቻላቸውም ፡፡
  • በብዙ ምክንያቶች ዋነኛው የመጠቅጠቅ ችግር መኖሩ ነው፡፡
  • በቀኝ በኩል ያለው አጥቂ በሁለቱም ቡድኖች ቢጠቀሙበት ትርፍ በማያገኙበት ቦታ ላይ ቆመዋል፡፡በቀኝ በኩል ያለው የመሀል ተጫዋች በአግድሞሽ ቡድኑ እንዳይጠቀጠቅ አድርጎታል ፡፡ይህ በሁለት ቁልፍ ቦታዎች ላይ የቁጥር ብልጫ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡ እነዚህም፡-
  1. የመጀመሪያው የቁጥር ብልጫ የሚፈጠረው የቀኝ የመሀል ተከላካዩ ነፃ በመሆን ኳስን በሚገፋበት ቦታ ላይ ይፈጠራል፡፡ይህም የ 4 ለ 3 የበላይነትን በመስመር በኩል ይፈጥራል(በሰማያዊ የተመለከተው)፡፡ይህም በዋናነት የተከሰተው ቡድኑ ቶሎ ቦታ መቀየር ስላልቻለ ነው፡፡በተለይም ሁለቱ አጥቂዎች ፡፡ይህ ደካማ የአግድሞሽ መጠጋጋት እንዲኖር አድርጓል፡፡
  2. በጣም አስፈላጊ በሆነው በመሀል ክፍል ቦታ ላይ የ 3 ለ 2 የበላይነት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡የቀኝ የመሀል ተጫዋቹ የመስመር ተመላላሹን በመያዝ የሚከላከለው ቡድን የአግድሞሽ መጠጋጋት(መጠቅጠቅ) እንዲያጣ አድርጓል፡፡

 

በምርጥ መጠቅጠቅ (መጠጋጋት) ቡድኑ ለኳሱ የተሻለ መዳረሻ በመያዝ ያተርፋል፡፡
  • በመሰረታዊ ደረጃ ቀላል የሆነው ወደ ኳሱ ቅርብ በመጠጋጋት ብዙ ተጫዋቾች ፕረስ ማድረግ በሚችሉበት ቦታ እንዲሆኑ ስለሚያስችል ለኳሱ የተሻለ መድረሻ እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡
  • ጥሩ የኳስ ተኮር እና ለፕረሲንግ የሚኖር ዝግጅት ኳሱ ላይ ውጤታማ ጫና ለማሳደር አስፈላጊ ናቸው፡፡

 

በደካማ መጠጋጋት (መጠቅጠቅ) ለኳሱ ደካማ መዳረሻ መያዝ ኳሱ የያዘው ቡድን የ 4 ለ 3 ቁጥር ብልጫ እንዲኖረው ያደርጋል ፡፡በዚህም ብዙ ቁጥር በሌለበት ቦታ ኳስን በመገልበጥ ዘልቆ ለመግባት ጊዜና ቦታ ያገኛል፡፡

 

በሌላ በኩል በተጠጋጋ (በተጠቀጠቀ) አደረጃጀት ቡድን ለኳሱ ጥሩ መዳረሻ እንዲኖረው በማድረግ ያተርፋል፡፡ኳስን በስልታዊ ደካማ ወደሆነው የሜዳ ክፍል በመውሰድ በቀላሉ ፕረስ ማድረግ ያስችላል፡፡

– የተጠጋጋ(የተጠቀጠቀ) ቅርፅን ጥቅም ላይ ስናውል (በተለይም የአግድሞሽ መጠቅጠቅን) የኳስ መዳረሻን መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

– ኳስ ላይ ጫና ሳይኖር ኳስ ቁጥጥራቸውን የሚረብሽ ምንም ስለሌለ ተቃራኒ ቡድን ኳስን ብዙ የተጫዋቾች ቁጥር በሌለበት ቦታ ለመገልበጥና ለመጠቀም ጊዜና ቦታን ሊጠቀሙ ይችላሉ ፡፡ከላይ በቀረበው ስዕል ለኳሱ ጥሩ መዳረሻ ሳይኖር ተከላካዩ ያልተረጋጋ በመሆን የቁጥር ብዛት በሌለበት በተቃራኒ አቅጣጫ የ 2ለ 0 ብልጫ እንዲኖር ያደርጋል፡፡

3 የአስፈላጊ ተጫዋች አለመኖርን መጠቀም

አስፈላጊ የሆነ ተጫዋች ማለት ምርጥ ኳስን በቅርብ የመቆጣጠርና የመግፋት ብቃት ያለው እና ቡድኑ በሜዳው በጣም ተጠግቶ ኳስ መቆጣጠር እንዲችል የሚያስችል ነው፡፡ይህም ከተከላካይ ከፍተኛ ጫና የሚኖርበት ቦታ ነው ፡፡በዚህም ምክንያት የተጠቀጠቀ መከላከል ባለው ቡድን በጣም ውጤታማ ናቸው፡፡

በዚህም እንደዚህ አይነት መከላከል ያለውን ቡድን በመልሶ ማጥቃት ለማጥቃት አስፈላጊ ናቸው፡፡ስለዚህም አስፈላጊ ተጫዋች የሌለውን ቡድን በዚህ መንገድ መጠቀም ያስችላል ፡፡

እንደ ምሳሌ መቅረብ የሚችለው ማድሪድና ባርሴሎና ከሲሞኒው አትሌቲኮ ጋር ሲጫወቱ ያለው ነው፡፡በተለይም ባርሴሎና የቴክኒካል ልህቀትያላቸው ተጫዋች ስላላቸው ፡፡በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆነው እንኳን በማጥቃት ላይ ያሉት ተጫዋቾች ኳስን መቆጣጠር ይችላሉ፡፡

4 የመገኛ ቦታን መቆጣጠር(spatial control)

በተራራቁት ተጫዋቾች መካከል በቁመትና በአግድሞሽ አጭር ርቀት እንዲኖር በማድረግ ቡድን ትንሽ ቦታ ይሸፍናል፤ግን ብዙ ይቆጣጠራሉ፡፡የተጠቀጠቀ ቅርፅ  በመያዝ ቡድን በሜዳው ላይ የተሻለ ቁጥጥር ይኖረዋል:: በሌላ በኩል ተራርቀው ከቆሙ የመገኛ ቦታ ቁጥጥሩን ባጣም የባሰ ይሆናል፡፡

የመገኛ ቦታ ቁጥጥር የሚኖረው በተጠቀሰው ቦታ የቁጥር የበላይነት ሲኖር ፤ይህም ተቃራኒ ቡድን  ይህን ቀጠና በማግኘት ለስልታዊ ትርፍ እንዳይጠቀምበት ማድረግ፡፡በቁጥር ብዙ መሆን የኳስ ማቀበያ መስመር መሸፈንን ያሻሽላል፣ጥቅምላይ ሊውል የሚችል ቦታን ይቀንሳል፡፡

የመገኛ ቦታ ቁጥጥር አስተዳደር ከኳስ በተቃራኒ ለመጠቅጠቅ ቁልፉ ነገር ነው፡፡በመከላከል ጊዜ በአብዛኛው ተቃራኒ ቡድን ስለማይጠቀምበት በሜዳው ላይ መሸፈን የሚያስፈልገን ቦታ አለ፡፡ይህም ከጎን  እና ከጎን ዘልቆ መግባት የማይችልበት ብዙ ምክንያት አለ፡፡ስለዚህም የሚከላከለው አስተዳደሩን ውጤታማ በማድረግ ቡድኑ ‹የጥጉን ቅርፅ›  በመተው ቁጥጥር የሚፈልገውን  በጣም አስፈላጊ የሆነውን ቦታ ይሸፍናሉ፡፡

ቀላሉና የተለመደው ጉዳይ የዚህ መከላከል አልፎ አልፎ እንደ ተቃራኒ ቡድን ቢለያይም በአትሌቲኮ 4-4-2 የዳር የመሀል ተጫዋቾቹ አጥብበው ይቆማሉ፡፡የሜዳውን ስፋት ከመሸፈን ይልቅ ወደ ውስጥ በመግባት በጣም አስፈላጊ የሆነውን የግማሽ -ክፍተቱን ይሸፍናሉ፡፡

የመከላከል ግድግዳወ ሰፊ ቦታ እየሸፈነ ነው፡፡ግን ቁጥጥር የለውም ፡፡

 

በዚህኛው ግን ትንሽ ቦታ ሸፍነዋል ግን ከፍ ባለ መመንገድ ተቆጣጥረውታል፡፡

 

ይህን ሰፋ ስናደርገው በተጠቀጠቀ የመከላከል ግድግዳ ቡድን በሜዳው የሆነ ክፍል ላይ ያተኩራል ፡፡በአብዛኛው ዋነኛው ቦታ በብዙ ምክንያት ትልቅ ስልታዊ ዋጋ ስላለው የመሀል ክፍሉን ይሆናል ፡፡

  1. ውጤታማ ያልሆነ የማጥቃት ስልትን መግፋት

መሀል ክፍሉን በመቆጣጠር ፣የተጠቀጠቀ መከላከል ተቃራኒ ቡድንን ውጤታማ ወዳልሆነ የማጥቃት ስልት ይገፋል -ተሻጋሪ ኳስ ፡፡መሀል ማጥቂያው ክፍል ሲያዝ ተቃራኒ ቡድን ያለው ብቸኛ አማራጭ ለመስመር ተከላካዮቹ መጫወት ብቻ ይሆናል ፡፡በአብዛኛው በእነዚህ ሁኔታዎች የመስመር ተከላካዮቹ ከጥልቀት ተሻጋሪ ኳስ ማቀበል ብቻ ይሆናል ፡፡ይህም ተሻጋሪ ኳስ ለመስጠት ምቹ ያልሆነው ቦታ ነው፡፡

 

 


የጽሁፉ ተርጓሚ አሰልጣኝ ደስታ ታደሰ ነው፡፡ አሰልጣኙ ባለፉት አስር ዓመታት በበጎ ፍቃድ ታዳጊዎችን በማሰልጠንና ለበርካታ ክለቦች በማበርከት እውቅና ባተረፈው የአስኮ እግር ኳስ ፕሮጀክት ሲያሰለጥን ቆይቷል ፡፡ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአፍሮ-ፂዮን እግር ኳስ ክለብ ከ17 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

error: