ወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

ከሰሞኑ የአሰልጣኙን ውል ለሁለት ተጨማሪ ዓመት ያራዘመው ወልቂጤ ከተማ አሁን ደግሞ አዲስ ተጫዋች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል፡፡

በዛሬው ዕለት ወደ ክለቡ ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ያለፉት ሦስት ዓመታትን በኤሌክትሪክ ያሳለፈው ዮሐንስ በዛብህ ነው። የቀድሞው የንግድ ባንክ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ ለወልቂጤ የፈረመ የመጀመርያ ተጫዋች ሲሆን በቅርቡ ቡድኑን ለቆ ፋሲል ከነማን የተቀላቀለውና በአጨዋወት ተቀራራቢ የሆነው ይድነቃቸው ኪዳኔን ቦታ እንደሚሸፍን ይጠበቃል ።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: