“ቅዱስ ጊዮርጊስን ማገልገል ለኔ ትልቅ ክብር ነው” አዳነ ግርማ

የእግርኳስ ጅማሮውን በሀዋሳ ከነማ አድርጎ በቅዱስ ጊዮርጊስ ገኖ መውጣት የቻለው ኮከቡ አዳነ ግርማ ዳግም ፈረሰኞቹን በአሰልጣኝነት ሊቀላቀል እንደሚችል መነገሩን ተከትሎ ለሶከር ኢትዮጵያ ሀሳቡን ገልጿል።

በኢትዮጵያ እግርኳስ በቅርብ ዓመታት ከታዩ ምርጥ አጥቂዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠራው አዳነ ግርማ ዛሬ በተጫዋችነት እና በም/አሰልጣኝነት ካገለገለው አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማ ጋር በስምምነት መለያየቱን ከሰዓታት በፊት መዘገባችን ይታወቃል። ይህን ተከትሎ በርካታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በተለያዩ መድረኮች አዳነ ዳግመኛ ወደ ፈሰኞቹ ቤት አሰልጣኝ ሆኖ እንዲመጣ ያላቸውን ፍላጎት ሲገልፁ ይሰማል። ከዚህ በተጨማሪ እኛም ባለን መረጃ የክለቡ አመራሮችም ቡድኑ በአሁኑ ወቅት አሰልጣኝ አልባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አዳነን በምክትል አሰልጣኝ ለመቅጠር ፍላጎት እንዳላቸው እየሰማን እንገኛለን። ይህን አስመልክቶ ለአደነ ግርማ ላቀረብነው ጥያቄ ተከታዩን አጭር ምላሽ ሰጥቶናል።

” እግርኳስን ስለማቆም አሁን ምንም ማሳብ አልፈልግም። ወደፊት የምናየው ነገር ነው። ከወልቂጤ ጋር የተለያየሁት በቤተሰብ የግል ምክንያት ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሰደብኩበት ፣ የደማሁበት ፣ ያደኩበት ፣ የጎለበትኩበት እና ብዙ ክብር ያገኘሁበት ቤቴ ነው። አሰልጣኝ ሁን የሚል ጥያቄ ከመጣ ምንም ለድርድር የማላቀርበው በሙሉ ልቤ የምቀበለው ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስን ማገልገል ለኔ ትልቅ ክብር ነው።”ብሏል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ