ምንይሉ ወንድሙ ወደ መቐለ ማምራቱ ሲረጋገጥ ሦስት ተጫዋቾችም ውላቸውን አራዝመዋል

መቐለ 70 እንደርታዎች ከቀናት በፊት በቃል ደረጃ የተስማሙት ምንይሉ ወንድሙን ሲያስፈርሙ በተመሳሳይ ውላቸውን ለማራዘም ተስማምተው የነበሩ ሦስት ተጫዋቾች ውልም አራዝመዋል።

ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በመከላከያ ቆይታ የነበረው እና በቆየባቸው ዓመታት በርካታ ግቦችን ያስቆጠረው አጥቂው ምንይሉ ወንድሙ ወደ መቐለ ለማምራት በቃል ደረጃ መስማማቱን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ወደ ሊጉ ማምራቱን ተከትሎ ከነፃነት ገብረመድኅን እና በረከት አማረ በመቀጠል ወደ ክለቡ የፈረሙ ተጫዋቾች ቁጥር ወደ ሦስት ከፍ አድርጎታል።

በተመሳሳይ በቃል ደረጃ ውላቸውን ለማራዘም ተስማምተው የነበሩት ሥዩም ተስፋዬ፣ አሚን ነስሩ እና ዮናስ ገረመው ውል መታደሱ ተረጋግጧል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ