ወላይታ ድቻ አማካይ ለማስፈረም ተስማማ

የጦና ንቦቹ ኤልያስ አሕመድን ስምንተኛ ፈራሚ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

የቀድሞው የሰበታ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ ተጫዋች የሆነው ኤልያስ ዘንድሮ ሊጉ እስከተሰረዘበት ጊዜ ድረስ በጅማ አባጅፋር በግሉ መልካም እንቅስቃሴን ሲያደርግ ቆይቷል። ውሉ በመጠናቀቁም ወደ የአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳውን ወላይታ ድቻ በሁለት ዓመት ውል ለመቀላቀል ዛሬ አመሻሽ ስምምነት ፈፅሟል፡፡

ወላይታ ድቻዎች እስከ አሁን ኤልያስ አሕመድን ጨምሮ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም መስማማት ችለዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: