ናይጄሪያዊው አጥቂ በዛሬው ዕለት ከመቐለ ጋር ለመቀጠል ፊርማውን አኖረ

ኦኪኪ አፎላቢ በዛሬው ዕለት ለተጨማሪ አመት በመቐለ 70 እንደርታ ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል፡፡

በ2010 ከጅማ አባጅፋር ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ያነሳው ናይጄሪያዊው አጥቂ ከዋንጫው ባሻገር በዛኑ ዓመት ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አጠናቋል፡፡ አወዛጋቢ በሆነ መልኩ ጅማን ለቆ ወደ ግብፁ እስማኤሊ አምርቶ ጥቂት ጊዜን ብቻ አሳልፎ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለመቐለ 70 እንደርታ ሲጫወት የነበረው አጥቂው ኢትዮጵያን ለቆ ወደ ሌሎች ክለቦች ያመራል ቢባልም ከሳምንት በፊት በቃል ደረጃ ከተስማማ በኃላ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ለአንድ ተጨማሪ ዓመት በመቐለ መቆየቱን አረጋግጧል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: