አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ የሰባት ነባር ተጫዋቾችን ውል ማደስ ችሏል።
ከትናንት በስትያ ቡድኑን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ላሳደጉ የሁለቱም ጾታ ቡድኖች ሽልማት ያበረከተው ሸገር ከተማ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር አዲሱን የወድድር ዓመት ለመቀጠል ከተስማማ በኋላ በትናንትው ዕለት ካሌብ በየነን ከአርባምንጭ ከተማ ማስፈረሙ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት የተጫዋቾቹን ውል ማደስ የገመሩት ሸገር ከተማዎች የፊት መስመር የግብ አዳኝ የሆነውን ከዚህ በፊት በባሌ ሮቤ እና በ ጋሞ ጨንቻ በ 2017 ደግሞ ከሸገር ከተማ ክለቡ ጋር ከፍተኛ ግብ በማስቆጠር የጨረሰው ያሬድ መኮንን እንዲሁም መነሻውን አምቦ ጎል ፊፋ ፕሮጀክት በመቀጠል በመከላከያ ተስፋ እና በጅማ አባጅፋር ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ወደ ሸገር ከተማ ተቀላቅሎ በ 2017 ጥሩ የውድድር ጊዜ ያሳለፈው የቀኝ መስመር አጥቂው አሚር አብዶን ጨምሮ ክለቡ የጀቤሳ ሚኤሳ ፣ ምስጋና ሚኪያስ ፣ ዘነበ ከድር ፣ አቤኔዜር ሕዝቅኤል እና ሙሉቀን ተስፋዬን ውል ማደስ ችሏል።