ፋሲል ከነማ ካሜሩናዊ ግብ ጠባቂ ለማስፈርም ተስማማ

ፋሲል ከነማ ካሜሩናዊ ግብ ጠባቂ ለማስፈርም ተስማማ

ዐፄዎቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የመጀመርያ ፈራሚያቸውን ለማግኘት ተቃርበዋል።

ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ከተለያዩ በኋላ የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ለመቅጠር ከጫፍ የደረሱት ዐፄዎቹ አሁን ደግሞ ባለፈው ውድድር ዓመት ከስሑል ሽረ ጋር በግሉ ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈውን ካሜሮናዊ ግብ ጠባቂ ሞየስ ፖዎቲ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በሀገሩ ክለብ ዩኒየን ዱዋላ የእግር ኳስ ሕይወቱ የጀመረው ይህ የሃያ ዘጠኝ ዓመት ግብ ጠባቂ ከዚህ ቀደም በዩናይትድ ስቴስት ሁለተኛ የሊግ እርከን በሚሳተፈው ኮሎራዶ ስፕሪንግስ ስዊችባክስ የሁለት ዓመት ቆይታ የነበረው ሲሆን ከዛ ቀጥሎ ለካሜሩኑ ክለብ ፎርቱና ደ ምፎው እንዲሁም ከ2022 ጀምሮ በጋናው አሻንቲ ኮቶኮ ከተጫወተ በኋላ ባለፈው የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በስሑል ሽረ ቆይታ ማድረግ የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ማረፍያውን ፋሲል ከነማ ለማድረግ ከጫፍ ደርሷል።