ተስፋ የተጣለበት ታዳጊ በባህር ዳር ይቀጥላል

ተስፋ የተጣለበት ታዳጊ በባህር ዳር ይቀጥላል

ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ድንቅ ብቃቱን ማሳየት የቻለው ታዳጊ በጣና ሞገዶቹ ቤት ለመቆየት ተስማምቷል።

ከባህር ዳር ተስፋ ቡድን መነሻውን ያደረገው እና ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ወደ ዋናው ቡድን ባደገበት ዓመት ድንቅ እንቅስቃሴን በማድረግ የአሰልጣኝ ቡድን አባላቱን እምነት ማግኘት የቻለው አማካዩ ሄኖክ ይበልጣል በባህር ዳር ከተማ ለተጨማሪ ዓመታት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የዓመቱ ተስፋ የተጣለበት ወጣት ተጫዋቾች እጩ ውስጥ መግባት የቻለው ተጫዋች በቀጣይ ዓመት በውሃ ሰማያዊዎቹ ማልያ የምንመለከተው ይሆናል።