ቅዱስ ጊዮርጊሶች ተጫማሪ ሁለት ተጫዋቾችን የግላቸው አድርገዋ።
በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ፈረሰኞቹ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ቡድናቸውን ለማጠናከር ወደ ዝውውር ገበያው የገቡ ሲሆን የአጥቂያቸውን ተገኑ ተሾመን ውል በማራዘም እንዲሁም አጥቂውን ቡአይ ኩዌት ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ አዲስ ተጫዋች ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።
በደቡብ ፖሊስ፣ ሲዳማ ቡና እና ያሳለፍነውን ዓመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ መጫወት የቻለው አማካዩ አበባየሁ ዮሐንስ በፈረሰኞቹ ቤት ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል። ሌላኛው ቡድኑን የተቀላቀለው የመስመር ተከላካዩ መሳፍንት ጳውሎስ ነው።