የመስመር ተከላካዩ በአሳዳጊው ክለብ ለተጨማሪ ሁለት አመት ለመቆየት ተስማማ።
አራት አመታትን በሲዳማ ቡና ቆይታ ያደረገው ደግፌ አለሙ ለተጨማሪ ሁለት አመት በቡድን ውስጥ ለመቆየት ስምምነት ላይ ደርሷል።
ከታዳጊ ቡድን ወደ ዋናው ካደገ በኋላ ላለፉት አራት አመታት በቡድን ግልጋሎት ሲሰጥ የነበረው የመስመር ተከላካዩ አንዳንዴም የፊት መስመር ተጫዋች ሆኖ የመጫወት ልምድ ያለው ተጫዋቹ ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት በአሳዳጊው ቡድን ውስጥ የሚያቆየውን ስምምነት ተፈራርሟል።
ተጫዋቾቹ ዘንድሮ ከሀያ አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት መጫወት መቻሉ ይታወሳል።