በቻምፒዮኖቹ ቤት ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ ብርቱካናማዎቹ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል።
የአብሥራ ሙሉጌታ፣ ጃፋር ሙደሲር ፣ አቤል ነጋሽ እና ሬድዋን ሸረፋን በማስፈረም የአማካዩ አቤል አሰበን ውል ለማራዘም እንዲሁም አስቻለው ታመነን ለማስፈረም የተስማሙት ድሬዳዋ ከተማዎች አሁን ደግሞ ያለፈው አንድ ዓመት ከመንፈቅ በኢትዮጵያ መድን ቆይታ የነበረውን የፊት መስመር ተጫዋቹ አብዲሳ ጀማልን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።
በ2016 የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሎ ከቡድኑ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያሳካው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር በድጋሚ ለመስራት ወደ ብርቱካናማዎቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል። ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በአርሲ ነገሌ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ እንዲሁም ከ2013 ጀምሮ ደግሞ በአዳማ ከተማ የአራት ዓመታት ቆይታ ማድረጉ ሲታወቅ አሁን ደግሞ በ2016 አጋማሽ ተቀላቅሎ በእግር ኳስ ሕይወቱ ለመጀመርያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያነሳበትን ኢትዮጵያ መድን ለቆ ወደ ምስራቁ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል።