ሲዳማ ቡናዎች የመሃል ተከላካዩን ለማስፈረም ተስማምተዋል

ሲዳማ ቡናዎች የመሃል ተከላካዩን ለማስፈረም ተስማምተዋል

ባለፈው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ንብ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ አሳዳጊ ክለቡ ተመልሷል።

ቅድመ ዝግጅታቸውን በሀዋሳ ከተማ ላይ የጀመሩት በዝውውር መስኮቱ የግብ ጠባቂውን መስፍን ሙዜ ፣ ደግፌ ዓለሙ ፣ ዮሴፍ ዮሐንስ እና ብርሃኑ በቀለ ውል ለማራዝም ተስማምተው ያሬድ ማቲዮስ ፣ ሞገስ ቱሜቻ፣ ተመስገን በጅሮንድ እና
አላዛር ማረነ ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉት ሲዳማ ቡናዎች አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ንብ ቆይታ የነበረው የቀድሞ ተጫዋቻቸው መኳንንት ካሳን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ከሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በዋናው ቡድን የሦስት ዓመታት ቆይታን በማድረግ በ2017 የውድድር ዘመን በከፍተኛ ሊጉ ንብ በመጫወት ያሳለፈው ወጣቱ ተከላካይ አሁን ደግሞ ወደ አሳዳጊ ክለቡ ተመልሶ ስብስቡን በመቀላቀል የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በማድረግ ላይ ይገኛል። የሁለት ዓመት ውል ይፈራረማል ተብሎ የሚጠበቀው ተጫዋቹ በቀጣይ ቀናት በይፋ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።