የቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊ ፍሬ የሆነው እና በከፍተኛ ሊግ ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈው አማካይ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተስማምቷል።
የመጀመሪያዎቹ አምስት ጨዋታዎች አዲስ አበባ በሚደረገው ውድደር የተደለደለው እና ከአስራ አምስት በላይ ተጫዋቾቹን ውል በማራዘም ግብ ጠባቂው ኢድሪሱ አብዱላሂ፣ ዳዊት ተፈራ፣ በረከት ወልዴ ፣ ሀቢብ ከማል እና አብዱልባሲጥ ከማልን ያስፈረመው ነገሌ አርሲ አሁን አማካይ ተስፋዬ በቀለን ለማስፈረም መስማማቱን አውቀናል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው ተስፋዬ ከፈረሰኞቹ ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ ከፍተኛ ሊግ በማምራት ለባቱ ከተማ ተጫውቶ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በቤንች ማጂ ቡና ጥሩ ቆይታ ያደረገ ሲሆን አሁን ማረፊያ ነገሌ አርሴ ሆኗል።