አክሲዮን ማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔውን ሊያደርግ ነው

አክሲዮን ማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔውን ሊያደርግ ነው

የሊጉ አክሲዮን ማኅበር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል።

ምስረታውን ካደረገ ስድስተኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን አውቀናል።

ስድስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ነገ ጥቅምት 2 ቀን በካፒታል ሆቴል ከጠዋቱ 02:00 ጀምሮ የሚያደርግ ሲሆን የ2017 የውድድር ዘመን አፈፃፀም እና የፋይናንስ ሪፖርት የሚደመጥ መሆኑ ሲሰማ በተጨማሪም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር የሚያደርግ ይሆናል።

አክሲዮን ማኅበሩ ከተመሰረተ ወዲህ ስድስት መደበኛ ሰባት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ከዚህ ቀደም ማድረጉ ይታወሳል።