ሀላባ ከተማ 21 ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሦስት ነባር ተጫዋቾችን ዉል ማደስ ችላል።
የ2018 ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ጅማ ከተማ በሚካሄደው ምድብ “ለ” የተደለደሉት በርበሬዎቹ ካለፈዉ ዓመት ከነበሩት ተጫዋቾች 3ቱን ብቻ በማስቀረት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።
ባለፈዉ ዓመት ከኢትዮጵያ መድን ጋር ቻምፒዮን የሆነዉ የቀኝ መስመር ተከላካዩ ያሬድ መሃመድ ፣ በወልዋሎ ዓ/ዩ የተወሰነ ጨዋታዎችን መጫወት የቻለዉ ሰለሞን ገመቹ ፣ በኢትዮጵያ ቡና ቤት ባደረጋቸዉ ጨዋታዎች ሁለት ግብ ማስቆጠር የቻለዉ እስራኤል ሸጎሌ እንዲሁም በረከት ወንድሙን ከሀዲያ ሆሳዕና ፣ ፀጋ ደርቤን ከደሴ ፣ ዳግም ሰለሞንን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ሚኪያስ ታምራትን ከደደቢት ፣ ታምራት በቀለን ከምድረገነት ሽረ ፣ ሙሉጌታ ካሳሁንን ከ አርባ ምንጭ ከተማ ፣ ብሩክ ቦጋለን ከደሴ ከተማ ፣ ምስክር መለሰን ከሸገር ግብ ጠባቂ አባቱ ጃርሶ ከሸገር ፣ አሊ ቡኖ ከሸገር ፣ ሚኪያስ ደጁ ከስልጤ ወራቤ ፣ ኪሩቤል ፍቅረ ማርቆስ ከሻሸመኔ ፣ መለሰ በለጠ ከአምቦ ፣ ሙሉቀን ተስፍዬ ከሸገር እና መለስ በለጠ ያስፈረሙት ሀላባዎች የፋሲል አበባየሁ ፣ የሰይድ ግርማ እና የአብዱከሪም ራመቶን ዉል አድሰዋል።