የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ10ኛ ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ እና አዳማ የሚካሄድ ሲሆን በቀጥታ ሥርጭቱ ዙሪያም አዲስ ዜና ሰምተናል።
የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ኦቢኤን እያስተላለፈው እንደሆነ ይታወቃል። ሆኖም ተቋሙ አዲስ አበባ ላይ የሚካሄዱ ጨዋታዎችን ብቻ ሽፋን እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን ሀዋሳ ላይ የነበረው ውድድር ወደ አዳማ ከተዛወረ በኋላ ሁለቱም ሜዳዎች ላይ የሚካሄዱ ጨዋታዎችን ለማስተላለፍ ጥረቶች እየተካሄዱ እንደሆነ አረጋግጠናል።

እስካሁን 45 ጨዋታዎች የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን ያገኙ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን በተለያየ ሜዳ የሚካሄዱ ጨዋታዎችም የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን ማግኘት ከቻሉ OBN ባለፉት አምስት ዓመታት የቀጥታ ሥርጭት አስተላላፊ ከነበረው ሱፐር ስፖርት የተለየ ሽፋን የሰጠ ተቋም ያደርገዋል።


