ለመጀመሪያ ጊዜ ዋልያዎቹን እንዲወክሉ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች እነማን ናቸው?

ለመጀመሪያ ጊዜ ዋልያዎቹን እንዲወክሉ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች እነማን ናቸው?

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዘመናዊ አሰራር በመከተል ለሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጨዋታ የሚሆኑ 23 ተጫዋቾችን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ሲያደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋናው ብሔራዊ ቡድን ደረጃ ጥሪ የደረሳቸው ተጫዋቾች እነማን እንደሆኑ እንደሚከተለው አዘጋጅተናል።

አሠልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌ በ2027 ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከሳኦቶሜ እና ፕሩንሲፔ ጋር የሚያደርጉ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊትም በጨዋታው የሚጠቀሟቸውን ተጫዋቾች በቀጥታ ስርጭት ይፋ አድርገዋል። በ23 ተጫዋቾች ዝርዝር ከነዓን ማርክነህ እና ጋቶች ፓኖም ከውጪ ሀገራት ክለቦች ሲመረጡ ቀሪዎቹ 21 ተጫዋቾች ከሀገር ውስጥ ክለቦች ተመርጠዋል። ከተመረጡት 23 ተጫዋቾች ለመጀመሪያ ጊዜ ዋልያዎቹን ለማገልገል ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾችም የሚከተሉት ናቸው (በዋናው ብሔራዊ ቡድን ደረጃ መሆኑ ልብ ይሏል)።

የመቻሉ አምበል ግሩም ሀጎስ፣ የወልዋሎ ዓ/ዩ አማካይ ብሩክ እንዳለ፣ አዳማ ከተማን ዘንድሮ የተቀላቀለው ብዙዓየሁ ሰይፈ እና ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ ዘንድሮ መቶ በነገሌ አርሲ እየተጫወተ የሚገኘው ካቤ ብዙነህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገራቸውን በዋናው ብሔራዊ ቡድን ደረጃ እንዲወክሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።