ኢትዮጵያዊያን ኢንተርናሽናል ዳኞች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለመምራት ተመድበዋል

ከአንድ ሳምንት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሚደረጉ መርሐግብሮች መካከል አንዱ የሆነው በጂቡቲ እና ደቡብ ሱዳን መካከል የሚካሄደው ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር በጂቡቲ ሜዳ ላይ እንዲደረግ ተወስኖ የነበር ቢሆንም ጂቡቲ የተፈቀደ የመጫወቻ ሜዳ ስለሌላት የደርሶ መልስ ጨዋታዋን እዛው የተጋጣሚዋ ሀገር ደቡብ ሱዳን ሜዳ ላይ ለማድረግ ወስናለች።
ይህንን የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ለመምራትም አራት ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ሲመረጡ ቴዎድሮስ ምትኩ በዋና ዳኝነት ፣ ሙስጠፋ መኪ እና ሲራጅ ኑርበገን በረዳትነት ፣ ዳንኤል ይታገሱ ደግሞ በአራተኛ ዳኝነት ወደ ስፍራው ለማምራት ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
* በ2026 የፊፋ ባጅ ካገኙ አዳዲስ ዳኞች መካከል የሆኑት ዳንኤል ይታገሱ እና ሲራጅ ኑርበገን የመጀመሪያ የሀገር ውጪ ውድድር የሚመሩ ይሆናል።

