የወላይታ ድቻ እና የነገሌ አርሲ የ34ኛ ሳምንት ብቸኛ ተስተካካካይ ጨዋታ የሚካሄድበት ሜዳ ታውቋል።
በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊደረጉ ከነበሩ ጨዋታዎች መካከል የወላይታ ድቻ እና የነገሌ አርሲ ፍልሚያ በዝናብ ምክንያት ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወሳል። የሊጉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ጨዋታው ሐሙስ ግንቦት 27/2018 በአዲስ አበባ እንዲደረግ መወሰኑ ይታወቃል።

አወዳዳሪው አካል የጨዋታው ቀን እንጂ ቦታው እና ሰዓቱን ያልገለፀ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባደረገችው ማጣራት ጨዋታው ነገ ዘጠኝ ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚከናወን አውቃለች።

