ወልዋሎዎች አማካዩን ለማስፈረም ተስማሙ

ወልዋሎዎች አማካዩን ለማስፈረም ተስማሙ

ሴኔጋላዊው የተከላካይ አማካይ ወደ ቢጫዎቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

ቀደም ብለው የተከላካዩ ነፃነት ገብረመድኅንን ውል ለማራዘም ተስማምተው ኢዮብ ዓለማየሁ ፣ በረከት ሳሙኤል እና ካርሎስ ዳምጠውን ያስፈረሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በአርባ ምንጭ ከተማ  የስድስት ወር ቆይታ የነበረውን ማማዱ ሴክ ለማፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ከዚህ ቀደም በሀገሩ ክለቦች ጀነሬሽን ፉት ፣ ቴውንጌትና ጃራፍ ጨምሮ በሞሮኮው ቴውታን ፣ ኤ ኤስ ቪታ እና አል ፎትዋ የተጫወተው ይህ የ29 ዓመት የተከላካይ አማካይ አሁን ደግሞ ከስድስት ወራት የአዞዎቹ ቆይታ በኋላ ወደ ወልዋሎ ለማምራት ቅድመ ስምምነት የፈፀመ ሲሆን ቀጣይ  ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ በይፋ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።