ወልዋሎ የመስመር ተጫዋቹን ውል አራዘመ

ወልዋሎ የመስመር ተጫዋቹን ውል አራዘመ

በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመሩት ወልዋሎዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል።

የነፃነት ገብረመድኅን እና ሰመረ ሀፍታይን ውል አራዝመው ኢዮብ ዓለማየሁ ፣ በረከት ሳሙኤል ፣ ካርሎስ ዳምጠው እና ማማዱ ሴክን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት እና በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙት የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ተሳታፊዎቹ ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ የመስመር ተጫዋቹ ስምዖን ማሩን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝመዋል። ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ ያለፉትን ሰባት ዓመታት አሳዳጊ ክለቡን ያገለገለው ስምዖን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለቡድኑ ጥሩ ግልጋሎት መስጠቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከነፃነት ገብረመድኅን እና አብሮ አደጉ ሰመረ ሀፍታይ ቀጥሎ ውሉን ያራዘመ ሦስተኛ ተጫዋች ሆኗል።