ወልዋሎዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

ወልዋሎዎች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የሚሳተፉት ቢጫዎቹ አማካዩን ለማስፈረም ተስማሙ

የአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ እንዲሁም የነፃነት ገብረመድህን ፣ ሰመረ ሀፍታይ ፣ ስምዖን ማሩና በየነ ባንጃን ውል ለማራዘም ተስማምተው አምስት አዳዲስ ተጫዋቾች ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ጋናዊው አማካይ መሐመድ ዓብዱል ባሲጥ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

ከዚህ ቀደም በሀገሩ ክለብ ካሬላ ዩናይትድ እና በጅቡቲው ጅቡቲ ቴሌኮም ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ወደ ቢጫዎቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል። በተጠናቀቀው ዓመት የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌደሬሽን እና ጎፈሬ የትጥቅ አምራች በጋራ ባዘጋጁት ውድድር ላይ ከክለቡ ጋር ተሳታፊ የነበረውና ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ የዕለቱ ኮከብ ሽልማትን ያገኘው አማካዩ ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ዓይን ውስጥ ቢገባም በወቅቱ ዝውውሩ ሳይሳካ ቀርቶ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ወልዋሎ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።