ያለፉትን አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ቆይታ የነበረው ቻርልስ ሙሴጌ ወደ ሌላ የሊጉ ክለብ ለመግባት ተቃርቧል።

በኢትዮጵያ በተስተናገደው የጣና ካፕ ውድድር ላይ ለዮጋንዳው ክለብ ሞደርን ጋዳፊ ሲጫወት ባሳየው ድንቅ ብቃት በድሬዎች ዐይን ገብቶ ፊርማውን በማኖር በብርቱካናማዎቹ ቤት አራት ዓመታት ቆይታ ካደረገ በኋላ በተጠናቀው የውድድር ዘመን በመቻል መጫወቱ የቻለው ዩጋንዳዊው ቻርለስ ሙሴጌ
ወደ ባህር ዳር ከተማ ለመቀላቀል መስማማቱን አውቀናል። የጣና ሞገዶቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የሽመልስ በቀለ፣ የኪቲካ ጅማ እና የዮዳሄ ዳዊትን ዝውውር መፈፀማቸው ይታወቃል።

