የሀብታሙ ታደሰ ማረፊያ ታውቋል

የሀብታሙ ታደሰ ማረፊያ ታውቋል

ከሲዳማ ቡና ጋር የሊጉ ዋንጫን ከፍ ያደረገው ሀብታሙ ታደሰ ቀጣይ መዳረሻው ሸገር ከተማ መሆኑ ታውቋል።

ከጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ የእግር ኳስ ህይወቱን መነሻ ያደረገው በመቀጠል ለወልቂጤ ከተማ፣ ለሀድያ ሆሳዕና፣ ለኢትዮጵያ ቡና፣ ለባህር ዳር ከተማ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሲዳማ ቡና ጋር ቆይታ የነበረው የመስመር አጥቂው ሀብታሙ ታደሰ ወደ ሌላው የሊጉ ክለብ ለማምራት ማረቡን አውቀናል።

የመስመር አጥቂውን ለማስፈረም ሸገር ከተማ ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ ያደረጉት ድርድር ወደ መስማማት በመድረሱ ፊርማውን ማኖሩን አውቀናል።