በአልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመሩት ሀዋሳዎች ስብስባቸው እያጠናከሩ ይገኛል።

በዝውውር ገበያው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች ብሩክ በየነ፣ ሙሴ ከቤላ እና ቃልአብ ውብሸት ፣ ሬድዋን ናስር እና ደስታ ዮሐንስን በማስፈረም እንዲሁም የብሩክ ታደለ እና ግብ ጠባቂ ምንተስኖት ጊንቦን፣ ግብ ጠባቂ ዳግም ተፈራ ፣ ናትናኤል ሻጋሞ፣ ሲሳይ ጋቾ፣ ዳዊት ታደሰ ፣ ፈቃደሥላሴ ደሳለኝ እና ቸርነት አውሽን ውል በማራዘም ወደ ዝውውር እንቅስቃሴ መግባታቸው ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ ተከላካዩን ንጋቱ ገብረሥላሴን ለማስፈረም መስማማታቸውን አውቃናል።
ከዚህ ቀደም በጅማ አባ ጅፋር እና በወላይታ ድቻ ያለፉትን ዓመታት ደግሞ በኢትዮጵያ መድን ቆይታ የነበረው ንጋቱ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወቃል። አሁን ለሁለት ዓመት ለመጫወት ለሐይቆቹ ፈርሟል።

