ሀድያ ሆሳዕናዎች ስብስባቸውን ማጠናከር ገፍተውበታል

ቀደም ብለው የአብዲ ዋበላው እና የቶሎሳ ንጉሴን ዝውውር ያጠናቀቁት በአሰልጣኝ ሳምሶም አየለ የሚመሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች ከሚያመጧቸው አዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል አያራዘሙ ሲሆን አሁን ደግሞ የአማካዩ ተፈራ አንለይን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት አራዝመዋል።
በመቻል ታዳጊ ቡድን መነሻውን ያደረገው አማካዩ ከዚህ ቀደም በለገጣፎ ለገዳዲ ተጫውቶ ያሰለፈ ሲሆን ወደ ሀድያ ሆሳዕና ከመጣ በኋላ በተሻለ እራሱን እያሳየ ሲገኝ አሁን ደግሞ ለአንድ ተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት መፈረሙን አውቀናል።

