በውድድር ዓመቱ ስምንት ግቦች ያስቆጠረው
ተስፈኛው ግብ ጠባቂ ወደ ዋናው ቡድን አድጓል

ከአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ጋር ለቀጣይ ዓመት ለመቀጠል የተስማሙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ወደ ዝውውሩ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ቡድናቸውን ለማጠናከር ሰፊ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ። አሁን ደግሞ ከ17 ዓመት በታች ጀምሮ እስከ 20 ዓመት ቡድን ድረስ ሲያገለግል የቆየው ተስፈኛው ግብ ጠባቂ ብሩክ ዘላለም ወደ ዋናው ቡድን አሳድገዋል።
ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ባለ ግራ እግሩ የግብ ዘብ ብሩክ ከግብ ጠባቂነት አቅሙ በተጨማሪ ከቆሙ ኳሶችን የቅጣት ምት እንዲሁም ፍፁም ቅጣት ምቶችን በማስቆጠር የሚታወቅ ሲሆን ዘንድሮ በተካሄደው ከ20 ዓመት በታች ውድድር ላይ በውድድር ዓመቱ አጠቃላይ ስምንት ጎሎችን አስቆጥሯል። ከዚህ ቀደም ከ17 ዓመት በታች ቡድን የዓመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኖ መሸለሙም ይታወሳል።

